የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ ከነስፌቱ (3 ሎቶች) አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች
ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች
ሎት 3 የደንብ ልብስ ከነስፌቱ
የአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን የ2019 ዓ.ም የበጀት አመቱን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት /TIN NO/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የሚወዳደሩበትን ናሙና /Sample/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራጮች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር/በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ስም CPO በማሰራት ከኦርጅናሉ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን መወዳደሪያ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 7/O-011 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ እየከፈሉ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ሰባተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7/O-06 በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸው፣ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡-ሜክሲኮ ሰንጋተራ ከዘመን ባንክ ጀርባ አዲስ ሲኒማ ማእከል
ስልክ ቁጥር ፡-0986878782-0911601556
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Cinema Houses Administration Enterprise invites bids for stationery, cleaning supplies, and tailored uniforms, split into three lots. Bidders must hold a renewed trade license, tax payment proof, TIN/VAT registration, and submit samples with their bid.
