ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 028/19 በግልፅ ጨረታ Fountain Solution፣ Round Bright Stiching Wire No 20፣ Gum Thermal CTP Plate እና Black Web Offset Ink አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 028/19
ድርጅታችን ለስራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ ግብአቶች ማለትም Fountain Solution ብዛት 3,000 ሊትር፣ Round Bright Stiching Wire No 20 ብዛት 2,000 ጥቅል፣ Gum Thermal CTP Plate ብዛት 1,000 ኪ.ግ እና Black Web Offset Ink 25kg ብዛት 5,000 ኪ.ግ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።
ጨረታው በ17/2/ 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት የቴክኒካል ሰነዳቸው ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
