አላቂ የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች ግዥ - የበንሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት (ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን)
የበንሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ብ/ክ/መ/ ምስራቃዊ ሲዳማ /ዞን/በ/ወ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽ/መሳሪያ እቃዎችን ባቀረቡት በግዥ ፍላጎታቸው መሠረት ሊገዛ ያቀደውን ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ፍቃድ ያሳደሱ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በፋይናንስ ህግ መሰረት 3% ዊዝሆልድ መክፈል የሚችሉ፤
- በተለያየ ምክንያት በዘርፉ ሥራ ላይ ዕገዳ ያልተጣለባቸዉ፤
- ተጫራቾች የጨረታዉን ማስከበሪያ 15000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማዝያዝ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታዉ ዋጋ ማቅረብያ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በበንሳ ወረዳ ገ/ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው መግዛት የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ ያለዉን ዋጋና ከቫት በፊት ያለዉን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት፤
- ተጫራቾች ጨረታዉን ካሸነፉ በኋላ የጨረታ ማስተካከያ መጠየቅ አይችሉም፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ላይ ዕቃ ዋጋ ከሞሉ በኋላ በአንድ ፖስታ ውስጥ ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾ የሚወዳደሩበት የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረዉ ከቫት በፊት ያለው ዋጋ በግለጽ መግለጽ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ጨረታ ካሸነፉ የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ዋጋ 10 ፐርሰንት በቼክ ወይም በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ እቃው የሚገዛው አይተም በአይተም ነው፤
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሰም በማሸግ በሁሉም ዶኪሜንት ላይ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20(ሀያ) ተከታታይ በስራ ቀናት ውስጥ የሚቆይ ሆኖ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 5:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን በበንሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 9 ላይ የሚከፈት ሆኖ የተጫራቾች አለመገኘት ግን የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ ጨረታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- የጨረታውን መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0916011436/0916361005
የበንሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Bensa Woreda Finance Office seeks legal suppliers for consumable stationery and office supplies, purchased item by item. Bidders must hold a valid trade licence, VAT registration and TIN, be on the suppliers list, and accept 3% withholding.
