Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)
  • Address ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፌሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251115500417
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline08 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500
  • Bid Securityብር 50,000.00 (CPO)
  • opening dateበዚሁ ቀን (መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም.) ከቀኑ 8:15
  • Categories Cleaning & Janitorial

ለዋና መስሪያ ቤት ቢሮ የ2019 ዓ.ም የፅዳት አገልግሎት ግዥ - የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (LP/OT/03/SIG/2019)

Ethiopian Sugar Industry Group (የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ)


የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ

የጨረታ ቁጥር LP/OT/03/SIG/2019

  1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ፊሊፕስ ህንፃ ላይ ለዋና መስሪያ ቤት አገልግሎት የሚጠቀምበትን ቢሮ ለ2019 ዓ.ም የፅዳት አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መፈፀም ይፈልጋል።
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018/19 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት/ የታክስ ክሊራንስ/ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን /መመዝገባቸውን/ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000000888862 ገቢ, በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መከፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2:00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00-11:00 ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

    የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
    ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
    አድራሻ አዲስ አበባ ልደታ ክ/ከተማ
    ጨለለቅ አልሳም ህንጻ ፊት ለፊት
    ፊሊፒስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
    ስልክ ቁጥር +251 11 5-51 6271
    አዲስ አበባ፣ኢትዮጵያ

  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:15 ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50.000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
  7. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለስላሳ (30) ቀናት ይሆናል።
  8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Sugar Industry Group seeks cleaning services for its head office at the Philips Building in Mexico area. Open to licensed, tax-compliant cleaning firms registered on the government suppliers list. Tender documents in Amharic.
Save Tender