በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2019 በጀት ዓመት ከታቀዱ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ስማርት ፖል መብራት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ አስተዳደር
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ጨረታ ቁጥር 002/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2019 በጀት ዓመት ከታቀዱ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች መካከል ስማርት ፖል መብራት ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መ/ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ በሽያጭ የሚቀርብ ስሆን ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸዉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ ከመንግስት ዕዳ ነጻ የሆነ፣
- የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው!
- የVAT ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው /TIN NO
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
- አሸናፊ ድርጅት መክፍል ያለበትን የሽያጭ ታክስ 3% ይከፍላል፡፡
- በጨረታ ላይ እንድሳተፉ ከገቢዎች ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ clearance/ ማቅረብ የምችሉ፣
- ድርጅቱ ሙሉ የስማርት ፖል የማምረት፣ የማቅረብ፣ የመትከል፣ ሙሉ ፓኬጅ አገልግሎት የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስክበርያ ያሸነፈበትን ገንዘብ ልከ 10% ያስይዛል፡፡
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን ከወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ በማይመለስ ብር 500 ብር /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
ዋጋ አቅራቢ ተወዳዳሪዎች የዕቃ ዓይቱንና ደረጃውን በሰነዱ ዝርዝር በተቀመጠው ቅደም ተከተል ሞልተው አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ቴከኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ለብቻውን እንዲሁም ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻው በማድረግ ሁሉንም በሰም በታሸገ በአንድ እናት ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ /CPO/ በባንክ በተረጋገጠ 100,000 ብር በፊደልም (አንድ መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ያለበት ሲሆን፤ /CPO/ ለብቻው ታሽጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ዶከመንት ጋር መቅረብ አለበት፡፡
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እየር ላይ ቆይተው በ16ኛው ቀን የሚከፈት ስሆን ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት በመሰብሰብያ አደራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ማሳሰቢያ፣ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0949159755/ 0932194807
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዲኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት
