Tender Detail

Tender Details


የአላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት፣ የቢሮ እቃዎች፣ ህትመት እና ቋሚ ዕቃዎች ግዥ – የቀበና ቅድመ አንደኛ፣ የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 04 የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚውሉ አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች ፣አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ለህትመት አገልግሎት፣ቋሚ ዕቃዎች እና ሌሎችም በ1ኛ ዙር ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች የተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ምዝገባ እና ፍቃድ ማስረጃ TIN No የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች ዋጋው ቫትን ጨምሮ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ዋጋውን ሞልተው ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ በቀበና ት/ቤት ስም
    1. ለደንብ ልብስ ተጫራች፡-ብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
    2. ለአላቂ የቢሮ እቃዎችና ለአላቂ የትምህርት እቃዎች ተጫራች፡-ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ)
    3. ለህትመት አገልግሎት ተጫራች፡-ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር ብቻ)
    4. ለሌሎች አላቂ እቃዎች ተጫራች፡-ብር 7,000.00(ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
    5. ለፕላንት፣ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ ተጫራች፡-ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር ብቻ)
    6. ለህንፃ፣ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዣ ተጫራች፡-ብር 7,000 (ሰባት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 300(ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይታሸግና 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲዋዋሉ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ናሙና ያልቀረበበት የዘገየ ጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ከጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በጨረታ ሰነድ 4.6 እና 9 የተቀመጡት ግዴታዎች ከሰነዱ ጋር ተሟልቶ ያላቀረቡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
  7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት እራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጀ ዕቃ ምርት ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ግብር ፈፅሞ መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ስርዝ ድልዝ መረጃዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  10. ት/ቤቱ ሰነዱ ላይ ካሰፈረቸው ውጪ ምንም ዓይነት የዋጋ፣የውድድር እና የቴክኖሎጂ አማራጮችን አይቀበልም፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ሰነዱ ላይ ዋጋ ሞልተው ሲያስገቡ የሚወዳደሩበት ሎት መጨረሻ ላይ የእቃዎቹ ጠቅላላ ድምር ዋጋ ይገለፅ፡፡

አድራሻ፡- ከቀበና አደባባይ ወደ ጀርመን ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ቤላ ገስት ሀውስ ጀርባ ላይ፡፡

ስልክ፡- 011 1 26 12 85

የቀበና ቅድመ አንደኛ ደረጃ፣የመ/ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for stationery, uniforms, cleaning and office supplies, printing services, and fixed assets via national open tender. Bidders must be VAT-registered with valid licenses, submit samples, and provide a 10% contract bond if awarded.
Save Tender