Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን
  • Address አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ፒያሳ/እስታቲክስ እናት ህንጻ ፊት ለፊት ዋስትና ንግድ ማአከል 15ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-27-68-25
  • Website
  • Deadline05 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200 ብር (non-refundable)
  • Bid SecurityLot 1: 10,000 ብር; Lot 2: 5,000 ብር; Lot 3: 5,000 ብር; Lot 4: 10,000 ብር; Lot 5: 5,000 ብር; Lot 6: 5,000 ብር; Lot 7: 5,000 ብር; Lot 8: 5,000 ብር; Lot 9: 10,000 ብር; Lot 10: 10,000 ብር (CPO)
  • opening date4፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Printing And Publishing

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን


ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 02/2019

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት

በ2019 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን (ቋሚ እቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች
  2. ሎት 2 የመኪኖች ማስዋቢያ እቃዎች
  3. ሎት 3 የህትመት አገልግሎት
  4. ሎት 4 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  5. ሎት 5 የጽዳት እቃ
  6. ሎት 6 የደንብ ልብስና ስፌት
  7. ሎት 7 ሌሎች አላቂ እቃዎች
  8. ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  9. ሎት 9 የመኪና ጎማ
  10. ሎት 10 የፈርኒቸር እቃዎች

መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ከገቢዎች የተጻፈ የአቅራቢነት ደብዳቤ ያላቸው፤
  5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tin No / ያላቸው፣
  6. በመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ (WWW.PPA.gov.et)
  7. ተጫራቾች የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO
    1. ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች 10,000 ብር
    2. ሎት 2 የመኪና ማስዋቢያ—5,000 ብር
    3. ሎት 3 የህትመት አገልግሎት—5,000 ብር
    4. ሎት 4 የቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 10,000 ብር
    5. ሎት 5 የጽዳት እቃዎች—5,000 ብር
    6. ሎት 6 የደንብ ልብስ———5,000 ብር
    7. ሎት 7 ሌሎች አላቂ እቃዎች--5,000 ብር
    8. ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና———5,000 ብር
    9. ሎት 9 የመኪና ጎማ ግዥ——10,000 ብር
    10. ሎት 10 የፈርኒቸር እቃዎች—10,000 ብር
  1. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር / ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለበት፤ እስፔስፍኬሽን ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ በተረጋጋ መንገድ ሞልተው ያስገቡ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 10 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15ኛ ፎቅ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 200 ብር ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡
  5. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ፋይናንሻል ኮፒ እና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ቴክኒካል ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል (ለየብቻ) በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ፤ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ በጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትግቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15ኛ ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
  7. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ
    1. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፤
    2. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ
  8. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው።
  9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፤ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ዘኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡
  2. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ክፍለ ከተማ፣ አራዳ ወረዳ 1 ፒያሳ እስታቲክስ ጎን ዋስትና ንግድ ማእከል እናት ህንጻ ፊት ለፊት 15ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-127-68-25 ይደውሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration Light Service Authority seeks bidders for consumable goods and services under 10 lots: stationery, car wash supplies, printing, electronics, cleaning materials, uniforms, tires, furniture, and more. Bidders must hold a valid trade license, TIN, VAT registration, and a supplier letter from Revenue. Samples and CPO required.
Save Tender