Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባህር ዳር
  • Address ባህር ዳር : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0582221100
  • Website
  • Deadline03 Oct 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Security2,000,000.00 (ሁለት ሚልዮን ብር)
  • opening date23/01/-2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Petroleum Products Fuel, Diesel , Oil And Lubricant , Machinery

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሸከርካሪና ማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት በጥቅል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለዉድድር ይጋብዛል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ባህር ዳር


የጨረታ ቁጥር-01/2019

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ለሚያከናውናቸው የመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውል የተሸከርካሪና ማሽነሪ ናፍታ፣ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ በሎት በጥቅል አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለዉድድር ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው፣

3. ተጫራቾች የሚጠበቅባቸውን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ።

4, የግዥው መጠን ከብር 500,000.00 አምስት መቶ ሺህ ብር በላይከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋርአያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

6. የሚገዙ የናፍታ፣ የተሽከርካሪና ማሽነሪ ዘይትና ቅባት ዓይነትና ዝርዝርመግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመ/ቤቱ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር1000013197966 በመከፈል የባንከ ዲፖዚት ስሊፕ በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 09 ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ 13/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 23/01/2019 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል፤

8. ማንኛውም ተጫራች የማጫረቻ ሰነዱን ማለትም ዋናና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በአንድ ኢንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ 

ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትርበሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት /በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ13/01/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ቀን 23/01/-2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

9.ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ መሆን አለበት ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዘይትና ቅባቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፣ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 2,000,000.00 /ሁለት ሚሊዮን ብር/ ብቻ ማስያዝ ይችላሉ፤

10.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ በቀን—/01/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 8፡30 ግዥ ኢፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፤

11. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ 12.ተጫራቾች በእያንዳንዱ የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና መህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድርውጭ ይደረጋል፡፡

13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-1100 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-322-5155 /058-222-1107 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

14. ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ባህር ዳር ፖ.ሣ.ቁ.382

አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
The Amhara Rural Roads Construction Agency seeks to buy diesel, oil, and lubricants for its road construction and maintenance vehicles and machinery via open tender. Bidders must have a valid trade license, TIN, tax payment proof, and VAT registration if the purchase exceeds 500,000 birr.
Save Tender