የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ ) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ በስከራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ ለሸገር ዳቦ መሸጫነት ሲያገለግሉ የነበሩ ባሶች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ኮፐር፣ የተለያዩ ንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ የህክምና እቃዎች፣ ጀኔሬተር፣ ሊፍት፣ የተቃጠለ ዘይት፣ የሞተር ፖምፕ፣ የላውንደሪ ማሽን) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስከራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች፣ ሸገር ባሶች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ለእያንዳንዳቸው ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር)፣ እንዲሁም የተለያዩ ያገለገሉ የንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ የህክምና እቃዎች፣ ከነመዳሪዎች) ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፈደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ ተጫራቾች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በአሃዝና በፈደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልግሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል፡፡
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በአንድ መለያ ቁጥር (መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሸያጭ የተዘጋጁትን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ የህክምና እቃዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ መስሪያ እቃዎች፣ ሊፍት፣ ጀኔሬተር፣ የአንዱን ቤት በአይነት የተቀመጡትን በጥቅል መጫረት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ ሌሎችን ንብረቶችን ደግሞ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ. ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል፡፡
- አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፣ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም፡፡
- በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን የሚጫረት ተጫራች ያሸነፈበትን በሙሉ ማንሳት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa City Administration is selling used vehicles, scrap vehicles, Sheger bread buses, scrap metal, copper, and assorted used property via open bid. Bidders must buy the tender document, bid for all items under a lot, inspect items before bidding, and submit a CPO bid security.
