Tender Detail

Tender Details

  • Company ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
  • Address , Phone: 00 00 00 00
  • Website
  • Deadline20 Oct 2026, 3:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (ብር አምስት መቶ ብቻ)
  • Bid Securityየጨረታ መነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንከ ከፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO)
  • opening dateበዛው ዕለት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ሰዓት
  • Categories Other Sales , Vehicle

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ንብ/019/2018

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. የተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች ከመስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በባንክ አካውንት ቁጥር ETB176400010001 የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ ብቻ) ገቢ በማድረግና ደረሰኙን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰንጋተራ ኮሜርስ ፊት ለፊት ራስ አበበ አረጋይ መንገድ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ሰፕላይ ቼይን አስተዳደር መምሪያ 26ኛ ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡
  2. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ የገዙበትን ደረሰኝ እና ጨረታ ሰነድ በመያዝ የተሽከርካሪዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ሪቼ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ የወደፊት ግንባታ ቅጥር ግቢ እና አራት ኪሎ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ ምድር ቤት ውስጥ በመገኘት ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 09 ቀን 2019 ዓም ከጧቱ 4:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት እንዲሁም በመጨረሻው ቀን ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት ብቻ መጎብኘት ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ያገለገለ ተሽከርካሪ ዓይነቱንና የሰሌዳ ቁጥር በትከከል በመጥቀስ የሚገዙበትን ዋጋ ሰነድ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት የባንኩ ሰፕላይ ቼይን አስተዳደር ቢሮ በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመላከ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ያገለገለ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በባንከ ከፍያ ማዘዣ ሲፒኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፤
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) 15% ጋር መሆኑ አለመሆኑን በግልፅ በሰነዱ ላይ በጽሁፍ ማመልከት ይኖርባቸዋል፤ ይህንን በግልፅ ያልጠቀሱ ተጫራቾች ካሉ ያቀረቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታከስ 15% ጋር እንዳቀረቡ ይወሰዳል፤
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልተያያዘበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ ከውድድር ውጪም ይሆናል፡
  7. ጨረታው ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በ 9:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንፃ 26ኛ ፎቅ በሰፕላይ ቼይን አስተዳደር መምሪያ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው ዝርዝር ውጤት በባንኩ እንደጸደቀ ለተጫራቾች ይገለጻል፤
  9. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊ ተጫራቾች ባንኩ ውጤቱን እንዳሳወቀ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች ግን ላሸነፉበት ተሸከርካሪ ሙሉ ከፍያውን ከፍለው ንብረቱን ካነሱ በኋላ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቶች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፣
  11. አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ያገለገለ ተሸከርካሪዎች ማሸነፋቸው በፅሁፍ ከተግለፀበት ዕለት ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ከፍያውን በመፈጸም ንብረቱን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤
  12. አሸናፊ ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ከፍያ በመፈፀም ንብረቱን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ባንኩ ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ለቆየበት በየቀኑ ብር 500.00 ለሃያ ቀን የሚያስከፍል ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካላነሱ ባንኩ ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል፡
  13. አሸናፊ ተጫራቾች በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከፍያውን ከፍለው ንበረቱን ካልተረከቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፤
  14. ለጨረታ የቀረቡት ያገለገለ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ወጪ፣ የስም ማዛወሪያ፣ ለመንግስት የሚከፈሉ የታከስ ከፍያዎችና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታ አሸናፊው ገዢው ይከፍላል፣
  15. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-50-44-52 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
  16. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 0116296246/0115512650

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

✨ messages.ai_summary
Nib International Bank invites bids to purchase various used vehicles sold as-is via open tender. Bidders must buy the tender document, may inspect vehicles at specified sites, and must submit bids with a 10% CPO bid security. Prices must state VAT inclusion. The bank may cancel the tender.
Save Tender