Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 11:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋው 1/4ኛ (CPO፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateህዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ምዝገባው እንደተጠናቀቀ
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Vehicle

የLifan X-60 ተሽከርካሪ (ኮድ 2-A27478 አ.አ) የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/መ/ቁ/137514 የፍ/አፈ/መ/ቁ/40775

የፍባለመብት እነ ወ/ሮ ትዕግስት ሙሴ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ማከዳ ሙሴ መካከል ባለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.137514 በቀን 10/6/2015ዓ.ም እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.150577 በቀን 28/11/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት መሰረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 07 YG የጋራዥ ውስጥ የሚገኝ የሰ/ቁ.ኮድ2-A27478 አ.አ Lifan x-60 ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,080,000 ( አንድ ሚሊዮን ሰማንያ ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 9 ቀን 2019ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ሲ.ሆን፤ እያንዳንዱ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A public auction by the Federal Courts Execution Office of a Lifan X-60 vehicle (code 2-A27478) located in a garage in Akaki Kaliti Sub-city, Woreda 07. Bidders must deposit a C.P.O. equal to one-quarter of their bid; the buyer pays transaction tax.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender