የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች የብረት ሼልፍ፣ ዋክስ(wax.350 gm)፣ ብረት ባለ 6 (Iron bar#6)፣ ብረት ባለ 8 (Iron bar=6)፣ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት (FDRE Refugees and Returnees Service)
ያገለግሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች የብረት ሼልፍ፣ ዋክስ(wax.350 gm)፣ ብረት ባለ 6 (Iron bar#6)፣ ብረት ባለ 8 (Iron bar=6)፣ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/በመክፈል እንቁላል ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ የፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ከፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይከዋለበት ከመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የከፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Gurantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከመስከረም 12 ቀን 2019 እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ባሉት የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥርግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ጨረታው ጉለሌ እንቁላል ፋብሪካ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን መስከረም 22 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋርየሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው፡፡
- በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭየመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251910474668 ወይም 251911569913 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
✨ messages.ai_summary
The Refugees and Returnees Service invites bidders to an open tender for the sale of assorted used items—metal shelves, wax (350 gm), iron bars #6 and #8—located at its head office compound near the Egg Factory and warehouse. Bidders must pay a non-refundable 200 birr for the sale document and submit a 2% CPO or bank guarantee.
