Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለመ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114708503
  • Website
  • Deadline30 Sep 2026, 9:45 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 100.00 (አንድ መቶ)
  • Bid Securityአምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO)
  • opening dateበዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Categories Other , Disposal Sale , Other Sales

በጉምሩክ ኮሚሽን ስ.ስ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ФТС 11/2019

በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


የእቃ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን ስ.ስ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ФТС 11/2019

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
  3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሐሙስ መስከረም 14 / 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመከፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
    ተ.ቁ የቅ/ጽ/ቤቱ ስም የጨረታ አይነት የንብረት መመልከቻ ቀን ከደሰዶነት ቀን ጀምሮ የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት
    1 አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሪክ ቅ/ጽ/ቤት የእቃ ግልፅ እስከ 19/01/2019 20/01/2019 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  6. የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
  7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ከላይ በተ/ቁ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
  10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ፡- 011-470-85-03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The Addis Ababa Kaliti Customs Branch Office seeks to sell various abandoned, seized, and contraband goods via open bid, including vehicle spare parts, mobile phones, electronics, home and office items, clothing, footwear, and cosmetics. Bidders must hold a valid trade license, TIN, VAT registration, and current tax clearance. Importers, owners, and their families may not participate.
Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

READ MORE