የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በባለቤትነት የያዛቸውን ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን 12 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ETHIOPIAN LOTTERY SERVICE (የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት)
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ኢሎስ/ያንስኮ/01/2019
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በባለቤትነት የያዛቸውን ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን 12 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የተሽከርካሪ ዓይነት | ሞደል (Model) | የተመረተበት ዓ.ም (GC) | የሰሌዳ (ታርጋ) ቁጥር (Plate No.) | የተሰጠው ኮድ | የመነሻ ዋጋ | የጨረታ ማስከበሪያ የመነሻ ዋጋውን 20% |
| 1 | ግሬትዎል ፒካፕ | CC103 1PS60 | 2011 | 4-17204 ኢት. | ELS-01-GW | 1,160,082.08 | 232,016.45 |
| 2 | ግሬትዎል ፒካፕ | CC103 1PS60 | 2011 | 4-17205 ኢት | ELS-02-GW | 1,160,082.08 | 232,016.45 |
| 3 | ግሬትዎል ፒካፕ | CC103 1PS60 | 2011 | 4-17206 ኢት | ELS-03-GW | 1,160,082.08 | 232,016.45 |
| 4 | ግሬትዎል ፒካፕ | CC103 1P560 | 2011 | 4-17230 ኢት | ELS-04-GW | 1,160,082.08 | 232,016.45 |
| 5 | ፎርላንድ የጭነት መኪና | BJ1043 V8JE6-2 | 2013 | 4-19447ኢት | ELS-05-FL | 545,318.89 | 109,063.80 |
| 6 | ፎርላንድ የጭነት መኪና | BJ1043 V8JE6-2 | 2013 | 4-19448ኢት | ELS-06-FL | 621,463.31 | 124,292.70 |
| 7 | ፎርላንድ የጭነት መኪና | BJ1043 V8JE6-2 | 2010 | 4-17530ኢት | ELS-07-FL | 448,672.91 | 89,734.60 |
| 8 | ሚትሱቡሽ ፒካፕ | K77TJENSI | 2005 | 4-11133ኢት | ELS-08-MP | 526,463.02 | 105,292.65 |
| 9 | ቶዮታ ሚኒባስ | YH60L B-JR | 1984 | 4-01665ኢት | ELS-09-TM | 25,508.73 | 5,101.75 |
| 10 | ጂሊ የቤት አውቶሞቢል | JL7100 AIU | 2007 | 4-40039 ኢት | ELS-10-GL | 322,367.49 | 64,473.50 |
| 11 | ሊፋን 520 የቤት አውቶሞቢል | LF7130 A | 2011 | 4-46001 ኢት | ELS-11-LA | 404,122.74 | 80,824.55 |
| 12 | አባይ የቤት አውቶሞቢል | HFC7130AG3 | 2009 | 4-46002 ኢት | ELS-12-AB | 391,203.21 | 78,240.65 |
የተሽከርካሪ ምልከታ
ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ከመስከረም 14/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 20/2019 ዓ.ም ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ብቻ ፒያሳ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ጎን በሚገኘው የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት ዘወትር በሥራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ8:00 እስከ 10:30 መመልከት ይችላሉ
የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ሁሉ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እስከ 8:00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሥም በተከፈተው የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000004652782 ገቢ በማድረግ ዋናውን የባንክ ገቢ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መሰሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 31 በአካል ቀርበው በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ስም የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን የእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ቀነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) ATA (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional bank guaranty) በማስያዝ ዋናውን ማስረጃ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
የጨረታ ማክፈቻ
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን የያዘ አንድ ዋና እና አንድ ቅጂ በተናጥል በፖስታ በማሸግ እንዲሁም በፖስታው ላይ ዋናውን ዋና ቅጂውን ደግሞ ቅጂ በማለት ለይተው በጉልህ በሚታይ ሁኔታ መጻፍ አለባቸው። ተጫራቹ ድርጅት ከሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣ ላለማጭበርበር ቃል የሚገባበት ቅጽ ሞልተው ማሕተምና ፈርማ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
ነገር ግን ተጫራቾች ለሰቦች ከህጉ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ኮፒ፣ የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ካርድ ኮፒ (ካለ) እና ላለማጭበርበር ቃል የሚጋባበት ቅጽ ሞልተው ማሕተምና ፈርማ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው። በአጠቃላይ በግልም ይሁን በድርጅት የሚቀርቡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸሁን አሟልታችሁ በማቅረብ እና የጨረታ ማስከበሪያውን ለብቻ በታሽክ ፖስታ በማድረግ እስከ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ እስከ 8:00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ ብቻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በመስከረም 21/2019 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ 8፡00 ሠዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 በኢትዮጵያ ሎተሪ ኣገልግሎት ዕድል አዳራሽ ተጫራቾች ወደሚገኙበት ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተሃኙበት ይከፈታል።
አገልግሎቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማስታወሻ ፣ ተጫራቾች ከመጫረታቸው በፊት ተሽከርካሪዎችን በ70 መመሰከትና ሁኔታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።
አድራሻ፡ አዲስ አበባ ፒያሳ እቴጌ ጣይቱ ሆቴል ጎን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት
ስልክ፡ +2510111266512 Els@org.et
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት
