Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
  • Address ኦሮሚያ ክልል፣ ኢትዮጵያ, Phone: 0472260145
  • Website
  • Deadline08 Oct 2026, 5:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) የማይመለስ
  • Bid Security15.000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO)
  • opening dateመስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. እስቴሽነሪ
  2. የብሮ ፈሮኒቸር
  3. የመኪና ጎማ ፊልትሮ ዘይት እና ፍሬን ሸራ
  4. የፅዳት ዕቃዎች
  5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  6. የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ጫማ

በዚሁ መሠረት-

  1. ተጫራቾች ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በአቅርቦት እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ከሠኮሩ ሀገር ውስጥ ገቢ /ጽ/ቤት በመከፈል ሠኮሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በማቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታው ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ እቃ 15.000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም (CPO) ከዋናው ቴክኒካል ሰነዱ ጋር በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ የእቃውን ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ Original & Copy በወረዳው ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. እቃዎቹ በጥያቄያችን መሠረት ደረጃቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
  7. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ዕቃዎቹን በጥራት ካላቀረበ ዕቃውን የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
  8. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት እቃውን እስከ ወረዳው ድረስ ማቅረብ ወይም ማድረስ ይኖርበታል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር የዕቃውን ብዛት ከማቅረቡ በፊት በ20% የመጨመር ወይም መቀነስ መብት አለው፡፡
  10. በመጨረሻ ወረዳው ወይም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-30-50-40-12, 09-35-15-20-72 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የሠኮሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Sekoru Woreda Finance Office seeks suppliers for stationery, furniture, vehicle tires, filters, oil, brake linings, cleaning supplies, electronics, and staff uniforms and shoes. Bidders must hold valid licenses, be tax-compliant, and registered for supply and VAT with supporting evidence. Items must meet specified quality standards and be delivered to the woreda.
Save Tender