የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ለ2019 የበጀት ዓመት ማዕከሉ ለሚመርታቸው የምርምር ዕቃዎችና ቴክኖሎጂዎች ግብዓት የሚውሉ ብረታ ብረቶች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ለወርክ ሾፕ ሥራ የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፣ በአጠቃላይ ለምርምር ሥራ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ለ2019 የበጀት ዓመት ማዕከሉ ለሚመርታቸው የምርምር ዕቃዎችና ቴክኖሎጂዎች ግብዓት የሚውሉ ብረታ ብረቶች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ለወርክ ሾፕ ሥራ የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፣ በአጠቃላይ ለምርምር ሥራ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊኖረው ይገባል።
- ለሚጠየቁ የግዥ ዕቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለቸውና በፌደራል ወይም በክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት /Suppliers list/ ያላቸውና የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No) ቲን ነምበር ዋናውን እና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ 1,000.00 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አሰላ በሚገኘው የማዕከሉ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት፣ ካልተገኙም በሌሉበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡45 ሰዓት በአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 ታዋቂ በሆነ ባንክ በ “CPO” ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0223311861 /0223312492/0930509164/0912263915 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል
