Tender Detail

Tender Details

  • Company በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ/ክ/ከ/ገ/ጽ/ቤት
  • Address ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913091660
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በCPO
  • opening dateበ16ኛው ቀን 4፡30
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ/ክ/ከ/ገ/ጽ/ቤት


ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች, ቋሚና አላቂ እቃዎች, የጽዳት እቃዎች, የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች, ፈርኒቸሮች, የመኪና ጎማዎች, የህንጻ መሳሪያዎች, የደንብ ልብሶች, የህትመት, ኤሌክትሮኒክስ እና የተሽከርካሪዎች ጥገና ስራዎች እንዲሁም የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት ትችላላችሁ።

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የተሰማሩበት ወይም ተጓዳኝ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ከሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚውል ከታወቀ መንግሰታዊ ባንከ ብር100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በCPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ መግዣ በሮቤ ከተማ አዶሼ ወለሼ ከፍለ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን ከሮቤ ከተማ አዶሼ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  5. በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሰረት እውቅና የተሰጣቸውን እቃዎች የሚያቀርብ መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. ፈርኒቸሮች፣ ኤሌከትሮኒክሶች፣የኮምፒውተር ቀለሞች ፣ቦርሳዎች ጨረታ ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ማቅረብ አለበት፡፡
  7. ለሰራተኞች ደንብ ልብስ የሚሆን ብትን ጨርቆች የተዘገጁ ልብሶችና የተለያዩ ቆዳ ጫማዎች ለከፋይ ምንጣፍና ለጨርቅ መጋረጃ እና ቀለሞች ናሙናዎች በሙሉ ለብቻ በፖስታ አሽገው ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና 1" እቃውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. በሰነዶቻቸው ላይ ሥማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡፡
  10. በተገለጹት የእቃ ዝርዝሮች አጠገብ በተቀመጡት ባዶ ቦታዎች ላይ የእቃዎችን ብራንድና ሞዴል በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በሚጫረቱት ሰነድ ላይ ከተገለጸው ስፔስፍኬሽን ውጪ በመሰረዝና በመደለዝ የራስን ስፔስፍኬሽን መጨመር አይቻልም; አማራጭ ካላቸው ግን የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት በመጥቀስ ለብቻ በሌላ ወረቀት ማያየዝ ይችላሉ፡፡
  12. ለሁሉም እቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው:፡
  13. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይቻልም፡፡
  14. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውንም ወጪ በመቻል መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  15. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታውን ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአገባቡ ሳይፈጸሙ ቢቀሩ ለውሉ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  16. የሚገዙ እቃዎች በተሰጠው ስፔስኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ኦሪጂናል ካልሆኑ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
  17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተከፍቶ ውሉ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግዢ መመሪያ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡
  18. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0912183527፣ደውለው ይጠይቁ፡፡

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የአዶሼ ወሼ ወለሼ ክ/ከ/ገንዘብ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for office supplies, furniture, cleaning materials, electronics, vehicle tires, building tools, uniforms, printing, repair works, and food services for sector offices under the 2019 budget. Bidders must hold valid trade licenses, VAT registration, and tax clearance.
Save Tender