የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ጽ/ቤቶች የሚውል፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የፅዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የየካ ከ/ከተማ የወረዳ12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ጽ/ቤቶች የሚውል፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የፅዳት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፦
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ለመሳተፍ እንዲችሉ የግብር ግዴታቸውን ስለመውጣቸው የተሰጠ የምስክር ወረቀት ለተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ እና በተጨማሪ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣ የሚቀርበው ሰነድ የሚታይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታይ የስራ ቀናት ክፍት መሆኑን እየገለፅን በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከታች በተገለፀው አድራሻ ጨረታው በሚዘጋበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፡፡ ዘገይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን የማይመለስ የሰነድ መሸጫ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ብር 15000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚመረቱበትን የእቃ አይነት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ሲያስገቡ ከቋሚ እቃ በስተቀር ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለ ናሙና የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አድራሻችን ኮተቤ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ ወይም ሰንሻይን መንደር ፊት ለፊት ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ዋ/የስራ ሂደት ክፍል ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
ስልክ ቁጥር 0118931691 በመደወል የሚፈልጉትን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፦ ተቋሙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው!
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, uniforms, and cleaning materials for budget offices under Yeka Sub-city District 12 Administration. Bidders must hold valid renewed business license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration certificates. Samples required for non-fixed items.
