የሰፈረ ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018ዓ.ም 1ኛ (አንደኛ) ዙር ግልፅ ጨረታ የሚፈልጋቸውን የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የትምህርት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ መፅሀፍት፣ የተለያዩ ዕድሳቶች፣ ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸሮች፣ ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ አይነቶች፣እና የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች አገልግሎቶች ግዢን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሰላም ቅድመ -አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰፈረ ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018ዓ.ም 1ኛ (አንደኛ) ዙር ግልፅ ጨረታ የሚፈልጋቸውን የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የትምህርት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ መፅሀፍት፣ የተለያዩ ዕድሳቶች፣ ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸሮች፣ ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ኤሌከትሮኒከስ አይነቶች፣እና የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች አገልግሎቶች ግዢን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚችሉ አቅራቢዎች፡-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በወቅቱ ከአቅራቢነት ያልታገዱ
- ቫት የተመዘገቡ እና የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ሁሉም ተጫራቾች ጨረታ አሸንፈ ዕቃ ሲያቀረቡ የገቢዎች ሚኒስቴር ባወጣዉ መመሪያ መሰረት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ የተተመዉ QR CODE ደረሰኝ ማቀረብ የሚችሉ መሆን አለበቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ በሚያቀርቡት ገንዘብ ዋጋ፡- በሎት የተቀመጡት የገንዛቡ መጠን በ1.5 እስከ 2 ፐርሰንት ተበዝቶ ነዉ የተቀመጠ ነው፡፡
| ሎት | የዕቃ ዓይነት | የብር መጠን (ሲ.ፒ.ኦ) |
| ሎት. 1 | አላቂ የቢሮ ዕቃዎች | 2500.00 |
| ሎት. 2 | ልዩ ልዩ የትምህርት መሳሪያዎች | 2000.00 |
| ሎት. 3 | ሌሎች ልዩ ልዩ መጠቀሚያ መሳሪያዎች | 2000.00 |
| ሎት. 4 | የፅዳት ዕቃዎች | 1000.00 |
| ሎት. 5 | ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ፈርኒቸሮች | 2000.00 |
| ሎት. 6 | ቋሚ ዕቃዎች የተለያዩ ኤሌክትሮኒከስ አይነቶች | 5000.00 |
| ሎት. 7 | የደንብ ልብስ | 2000.00 |
| ሎት. 8 | የደንብ ልብስ ስፌት | 1500.00 |
| ሎት. 9 | የስፖርት መምህራን ትጥቅ | 2000.00 |
| ሎት. 10 | የህትመት አገልግሎት | 1000.00 |
| ሎት. 11 | የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች | 3000.00 |
| ሎት. 12 | የተለያዩ የላብራቶሪ ዕቃዎች | 2000.00 |
| ሎት. 13 | የተለያዩ ፕላንትና ማሽነሪ ዕድሳትና ጥገና | 1500.00 |
| ሎት. 14 | ለህንፃና ቁሳቁስ ተገጣጣሚዎች ዕድሳትና ጥገና | 2000.00 |
- የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10(አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሠፈረ ሠላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና በግዢ ቢሮ ለዙሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተህ በማሳረፍ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ከፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውን እና ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ሰነዶች እና በባንከ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) በአንድ ላይ በማሸግ ኮፒዎችንም ለየብቻ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ወይም ናሙና ለማቅረብ ለማያስፈልግ ለብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻ በትክከል በመሙላት ሁሉንም ሰነዶች በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እና የዋጋ ማቅረቢያው ሳይለወጥና ሳይቀነስ በሙሉ የማይመልስ አቅራቢ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ በስራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ በምታመርቱት ምርት ላይ ብቻ ልዩ አስተያየት ስለምናደርግ አምራች መሆናችሁን ካደራጃችሁ አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ጨረታው የሚያበቀዉ በ10ኛ ቀን እስከ 11፡30 የሚያበቀ ይሆናል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያውኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል! ከኛው ቀን ስራ የሌለበት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ 2(ሁለት) ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ወይንም ስፔስፊኬሽን ስለ ዕቃው በደንብ በሚገልፅ መልኩ ተዘጋጅቶ ማቅረብ መቻል አለባቸው! የናሙና መቀበያ ቅፅ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ የድርጅቱን ማህተብ በማድረግ አብሮ ማቅረብ መቻል አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ያለ ስርዝ ድልዝ በትከከል መሞላት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የማይነበብ እና ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ከ/ከ ወረዳ 4 ፅ/ቤት ፊት ለፊት በድሮው ጭማድ በአዲሱ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፊት ለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ የሰፈረ ሰላም ቅድመ-አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0112733497፣ 0112136221፣ 0112135898
ሰላም ቅድመ -አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for supply of cleaning items, office supplies, uniforms, educational tools, books, renovations, furniture, electronics, and musical instruments. Bidders need valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration. Tender documents available for purchase.
