Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 01133810035
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 10:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር
  • Bid Security2% በባንክ በተመሰከረ CPO
  • opening dateበ16ኛ የስራ ቀን 1. በዛኑ ቀን 4፡ 30 ይከፈታል፡፡
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

አንደኛ ዙር ለ2019 ዓ.ም የበጀት አመት በወረዳው ለሚገኙት መ/ቤቶች፡ የደንብ ልብሶች የጽዳት እቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ፤ የኤሌከትሮኒከስ እና ፈርኒቸሮች የመኪና እና የሞተር ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የተወዳዳሪዎች መስፈርት

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ግዴታ የተወጡ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተረሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነው መቀበል አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ/ ብር በመከፈል ከሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይቻላል፡፡
  7. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች በተገኙበት 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዛኑ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተወዳደሩበትን የእቃ ብዛት ተባዝቶ 2% በባንክ በተመሰከረ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ ብቻ መሆን አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  10. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች በፈለጉትና ማቅረብ በሚችሉት ዕቃዎች ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ አሸናፊ ተጫራች ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት እስከ 7ኛ ቀን ቀርቦ ውል ካልፈረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ይወረስበታል።
  12. ያሰቀመጥነው ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ መጨመር እና መቀነስም ይቻላል፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታ ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎችን ሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታው ላይ ባይገኙም ጨረታውን መከፈት አያግድም፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡ ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምዕራብ የምትገኘው ሰበታ ከተማ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /0912245947/01133810035

የሰበታ አዋስ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for the supply of uniforms, cleaning supplies, office equipment, electronics, furniture, and vehicle/motor tires to district offices. Bidders need a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier certification.
Save Tender