የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥ
የጎንደር/መም /ትምህርት ኮሌጅ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆነ ለዚህ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ከ1 እስከ 2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ03/12/2018 ዓ.ም እስከ 18/12/2018 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 19 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተጫራቹ የሞላውን ጠ/ዋጋ 1% CPO በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በአማርኛ የተተረጎመ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በጎንደር መም/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ የስራ ሂደት ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት ከ03/12/2018 ዓ.ም እስከ 19/12/2018 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ዕለት 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 01 በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ውድድሩ (አሸናፊ) የሚለየው በጠቅላላ ወይም በነጠላ ዋጋ ሊሆን ይችላል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ጎ/መ/ት/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር G1 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0581121634 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጎንደር/መም /ትምህርት ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
- Open tender for the procurement of construction/building materials, issued by Gondar Teachers' Education College (Amhara region).
- Bidders must have a renewed business license and TIN for the current year; VAT-registered bidders must present a VAT registration certificate.
- Bid bond: 1% CPO of the bid price, secured via bank-confirmed CPO or an unconditional bank guarantee translated into Amharic.
- Tender documents are available from 03/12/2018 E.C. to 18/12/2018 E.C. during working hours; bids must be submitted by 19/12/2018 E.C. at 3:30, with opening the same day at the college.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
