የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ ለሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለጸውን እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 08/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ ለሥራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተገለጸውን እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
· ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ግዥ
· ሉት 2 የክው ማኔጅመንት ሲስተም ዕቃዎችና አገልግሎትና ዝርጋታ ግዥ
በዚሁ መሠረት-
1. በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የገበረ
2. የቫት (VAT) ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያለው
3. የግብር ከፋይ /TIN/ መለያ ቁጥር ያለው
4. የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው አካዉንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስሊፕ ይዞ ሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 230 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ በCPO /Bid Bond የ90 ቀን/ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ/ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችል፡፡
8. ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና 2 ኮፒ በተለያየ በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና ኮፒነ በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ 8፡45 ሰዓት ላይ ተጫራቾች / ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል / የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።
10. የጨረታ አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዝን ማስገባትና ሰነዱ ላይ በተገለጸዉ መሰረት አገልግሎቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
11. የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0462125584
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
