የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚልሻ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማለትም ዴስክቶፕ ኮምፒዉተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ እና L.C.D.ፕሮጀክተር እዲሁም ሞተርሳይክል እና የሞተር ሳይክል ጎማ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሚልሻ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማለትም ዴስክቶፕ ኮምፒዉተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ እና L.C.D.ፕሮጀክተር እዲሁም ሞተርሳይክል እና የሞተር ሳይክል ጎማ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-
1. በግብር ከፋይነት ተመዝግበዉ የአቅራቢነት ሠርትፍኬት ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸዉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆነዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታ መሳተፍ የሚችሉበትን የግዜ ገደብ የሚገልፅ ከሚመለከተዉ አካል ማስረጃ በመያዝ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ተከታታይ በሥራ ቀናት በሲዳማ/ብ/ክ/መን ሚልሻ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የዉል ማስከበሪ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ወይም በስተጀርባ ሕጋዊ የባንክ ማህተም ያረፈበት ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ እንቨሎፕ ዉስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ይያያዛል።
3. ይህ ጨረታ በ16ኛዉ የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ የጨረታ መክፈቻ ዕለት በተጠቀሰዉ ሰዓት በሚቀጥለዉ በሥራ ቀን ይሆናል።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻ በግልፅ በመሙላት በማህተምና በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። አንዱ ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
5. ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸዉ የሚፈፀም ማንኛዉም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
6. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
አድራሻ
ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፊት ለፊት ትንሽ አለፍ ተብሎ ባለዉ ግቢ ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 5 ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሚልሻ ጽ/ቤት ስልክ ቁ.046 212 4273
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሚልሻ ጽ/ቤት
