የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ንግድ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት በጨረታው ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አቅርቦት ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ በእቃ አቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ /TIN/ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ሂሳብ ቁጥር 1000026941737 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ የግ/ን/አስ/ደ/ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራች ለውድድሩ የሚያቀርቡት የጨረታ ዶክመንት ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ሕጋዊ ባንክ የተረጋገጠ የብር /20,000/ ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ CPO በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ስም አሠርቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውሉን ማስከበሪያ አሸናፊ ከሆነባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ከኮሌጁ ከሚገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ በመሙላት ዋናው /ኦርጅናል/ እና ኮፒው ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው በፖስታው ላይ የኮሌጁ ስም እና ጨረታ ቁጥር በመፃፍ የንግድ ድርጅቱ ስም እና ማህተም በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
7. ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ ለውድድሩ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርበው ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ላይ ብቻ ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክመንት ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መደረግ አለበት፡፡
8. ተጫራቾች ከጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ጨምሮ ማንኛውም መረጃዎች ለውድድር ከሚያቀርቡት ኦርጅናል የጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
9. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ይከፈታል፡፡ ጨረታ የሚከፈትበት እለት በዓል ወይንም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
10. አሸናፊው ውል ተፈራርሞ ካጠናቀቀበት ጊዜ አንስቶ በ07 ቀናት ውስጥ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮሌጁ ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል።
11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡
12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ሁኔታ ቫትን የተጨማሪ እሴት ታክስ /ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ተበሎ ይወሰዳል።
13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-በስ.ቁጥር 011 365 8463/0113301624 ደደውሉ፡፡
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅና ሳተላይት ካምፓስ
