አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በድጋሚ የወጣ ሎት 01 የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች በድጋሚ የወጣ፣ ሎት 02 ጅኦምብሬን እና የዉሃ እቃዎችን፣ ሎት 3 የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ ሎት 04 ፓምፕና የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች፣ በድጋሚ የወጣ ሎት 05 የተሸከርካሪ ጎማ እና ሎት 06 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች (ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ እን ዲስክ ቶፕ ኮምፒውተር)፣ ሎት 07 የተቀናጀ የሀብት አስ
Abay Construction (አባይ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አኮኃ/የተ/የግ/ማ / ብግጨ /ዕ7-03/18
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በድጋሚ የወጣ ሎት 01 የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎች በድጋሚ የወጣ፣ ሎት 02 ጅኦምብሬን እና የዉሃ እቃዎችን፣ ሎት 3 የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ ሎት 04 ፓምፕና የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች፣ በድጋሚ የወጣ ሎት 05 የተሸከርካሪ ጎማ እና ሎት 06 የኤሌክትሮኒክ እቃዎች (ላፕቶፕ፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ እን ዲስክ ቶፕ ኮምፒውተር)፣ ሎት 07 የተቀናጀ የሀብት አስተዳደር ልማት ማበልፀግ (ERP Automation for construction company) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ድርጅቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
2. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ ቤተክርስቲያን ህዳሴ ሰፈር ታክስ ማዞሪያ 190 ሜትር አልፍ ብሎ አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ከግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል።
4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንከ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት በስራ ሰዓት ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
6. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል።
7. 15ኛው ተከታታይ ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
8. አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም htps://www.abayconstruction.org.et/auction-bid/ ማግኘት ይቻላል።
10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918216183/0918727684 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
