Tender Detail

Tender Details

  • Company በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
  • Address ሸገር ከተማ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ 44 ማዞሪያ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-84-62-79
  • Website
  • Deadline22 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-22 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Energy, Power And Electricity , Electrical Materials

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ቮልቴጅ ፕሮቴክተር ፈርም ዌር (Voltage Protector firmware) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ቮልቴጅ ፕሮቴክተር ፈርም ዌር (Voltage Protector firmware) በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትጫረቱ ተጋብዟችኋል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት እንድሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ጨረታወ- ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺ ከ00/100) ለብቻው በፖስታ አሽገው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

4.     ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላትና በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።

5.     በተጫራቾች የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፤

6.     ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሳ) ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለገጣፎ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር 1000692062144 ገቢ በማድረግ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች የጨረታ የሰነዱን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8.     ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዱን ለየብቻ ለይቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 (ሰላሳ) ቀናት አየር ላይ ውሎ በ31ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪያችን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

11. ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ለስልሳ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ስለሆነ ተጫራቾችም ይህን ታሳቢ አድርገው ስለመቀበላቸው በሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ አለባቸው።

12. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ፡- ሸገር ከተማ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ 44 ማዞሪያ ለገዳዲ ውሃ ማጣሪያ አጠገብ ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥራችን 09-13-84-62-79 /09-10-27-43-08 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

Save Tender