በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት የደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ፋይ/ፕ/ጽ/ቤት ቀላል መኪናዎች፣ ያገለገሉ የውሃ ፓምፖች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች፣ ያገለገሉ ጀነሬተሮች እና የተለያዩ ቀላልና ከባድ ብረታ ብረቶች እንዲሁም የሞተር ጀልባ ኢንጂኖችን በሐራጅ ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ዘዴ መሸጥ ይፈልጋል።
የዳሰነች ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ኦሞራቴ
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግሥት የደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ፋይ/ፕ/ጽ/ቤት ቀላል መኪናዎች፣ ያገለገሉ የውሃ ፓምፖች፣ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች፣ ያገለገሉ ጀነሬተሮች እና የተለያዩ ቀላልና ከባድ ብረታ ብረቶች እንዲሁም የሞተር ጀልባ ኢንጂኖችን በሐራጅ ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ዘዴ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛዉም ተጫራች በጨረታዉ ላይ መወዳደር ይችላል።
1. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም የታደሰ ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰላሳ /30/ ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 200 / ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የዕቃዎችን ዝርዝር መረጃ፣ መነሻ ዋጋ እንዲሁም የተጫራቾች መመሪያ የያዘ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በዳ/ወ/ም/ቤት አደራሽ ይከፈታል።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከገዙ በኋላ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎችን ራቴ ችግኝ ጣቢያ ዛፍ ስር ያለውን መኪናና ወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ያለውን ዕቃ በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20/ሃያ በመቶ/የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ CPO/ በማዘጋጀት ከጨረታዉ መክፈቻ ቀደም ብሎ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. መስሪያ ቤቱ በአማራጭ፣ በጅምላም ሆነ በችርቻሮ መሸጥ ስለሚችል ተጫራቾች እንደ ፍላጎታቸው የመነሻ ዋጋ ላይ የራሳቸውን ዋጋ በነጠላም ሆነ በጅምላ ድምር በማስቀመጥ መወዳዳር ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የግብር እዳ ካለ በባለንብረት መስሪያ ቤቱ የሚሸፈን ሲሆን የስም ማዛወር፣ የትራንዚት፣ የጉሙሩክ ቀረጥ እና ሌሎች ወጭዎች ግን በገዥው የሚሸፈኑ ይሆናል።
7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስኪወስዱ ድረስ ለውል አተገባበር ዋስትና የሚሆን ጠቅላላ ዋጋውን 20%/ሃያ በመቶ / በማግስቱ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከታወቀ ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁንና ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰዉ የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል።
9. መስሪያ ቤቱ የጨረታ ሰነዱን በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረን ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ያደረጋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረቶች አጠቃለው በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን የማያነሱ ከሆነ ንብረቶቹ ለመንግስት ገቢ በማድረግ ይወረሳሉ።
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09-16-87-30-33 / 09-12-73-87-75 ወይም 09-13-10-96-88
የዳሰነች ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ኦሞራቴ
