Tender Detail

Tender Details


የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ዘመን በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

Arba Minch College Of Education (የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ)


የጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ዘመን በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ግዥዎችን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ግብር በመክፈል ፈቃድ ያሳደሱ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የቲን ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ከላይ የተገለፀው መስፈርት የምታሟሉና በተጠቀሰው ዘርፍ የተሰማራችሁ ነጋዴዎችና ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ወደ ኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብረት አስተዳደር ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ በማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ናሙና እንዲቀርብ በተጠየቁ ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አንድ ቀን ቀድም ብሎ ለኮሌጁማቅረብ አለባቸው::  

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

ጨረታው አየር ላይየሚቆይበት ጊዜ

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ናሙና የተመረጠበት

1

የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች

15ቀን

16ኛው ቀን

3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል

 

2

የጽዳት ዕቃዎች

16ቀን

17ኛው ቀን

3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል

ናሙና ያስፈልጋል

3

የጽህፈት መሣሪያ

17ቀን

18ኛው ቀን

3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል

ናሙና ያስፈልጋል

4

የደንብ ልብስ

18ቀን

19ኛው ቀን

3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል

ናሙና ያስፈልጋል

5

የመኪና ጎማ

19ቀን

20ኛው ቀን

3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል

 

6

የኮስትር መኪና ጥገና

20ቀን

21ኛው ቀን

3:30 ታሽጎ 4:00 ይከፈታል

 

በቀረበው ናሙና ዕቃ ላይ ጥራቱ በባለሙያዎች ተረጋግጦ ያለፈ የናሙና ዕቃ ዋጋ ይነበባል። ከላይየተዘረዘሩት ሁሉም የግዥ አይነቶች የጨረታ ዋጋ በየዘርፉ ተሞልቶ ዋናውና ኮፒውን በሁለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ ስልከና ፊርማ በማድረግና በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ መክፈቻ ቦታው በአርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ለ60 ቀን የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ/Bid bond/ በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ ወይም /CPO/ 10,000 /አስር ሺህ/ ብር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ እስከ ኮሌጁ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

 

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0468812071 ደውለው ይጠይቁ፡፡

አርባ ምንጭ ትምህርት ኮሌጅ

Save Tender