Tender Detail

Tender Details


አኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ላፕቶፕና ተያያዥ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AMFI 07/2018

 

አኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ ላፕቶፕና ተያያዥ የቢሮ እቃዎች

 በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፣

1.     ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለሥልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2.     ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በተከፈለበት በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ደረሠኝ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 300.00 (ሦሥት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ በአሐዱ ባንክ ሐሳብ ቁጥር 0003230410101 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

5.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ትከክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡

6.     አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

7.     ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

8.     የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡

9.     ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011 637 66 68 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር

Save Tender