Tender Detail

Tender Details


በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በ2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት


የ2ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በ2ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የግዢ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም ሎት 1/ አላቂ የጽሕፈት ዕቃዎች ፣ ሎት2/ አላቂ የትምህርት አቃዎች፤ ሎት 3/ አላቂ የፅዳት እቃዎች፤ ሎት 4/ የተለያዩ የህንፃ እና የጥገና እቃዎች፣ ሎት 5/ቋሚ እቃዎች ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1.       የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ቲን/ቁ ማቅረብ የሚችሉ

2.       የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.       የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በተወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።

4.       የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

5.       ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፣

6.       ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ለተጠየቀባቸው እቃዎች የጨረታ ሰነዶችን ሲያስገቡ የተገለፀውን ዋናውና የማቅረብ ግዴታ አለበት።

ለተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1/ አላቂ የጽሕፈት እቃዎች 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ሎት 2/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 3000 (ሁለት ሺህ ብር) ሎት 3/ አላቂ የፅዳት እቃዎች 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ሎት 4/ የተለያዩ የህንፃ እና የጥገና እቃዎች 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ሎት 5/ቀሚ እቃዎች 4000.00 (አራት ሺህ ብር)

7.       በባንከ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8.       ተጫራቾች ለጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

9.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይ/ግዢ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል እና ኮፒውን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ተቋሙ የሸጠው ሰነድ መመለስ አለባቸው ከዛ ውጪ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

10.   ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ነገር ግን ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን የሚገልፅ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

11.   የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን እቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ደኖርባቸዋል።

12.   የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 በት/ቤቱ ፋይ/ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል።

13.   ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

14.   ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፤፤

አድራሻ፦ ከኬንያ ኢምባሲ 500 ሜትር ወደ ላይ በሚወስደው አስፓልት ገባ ብሎ ዳዊት ጋራዥ አጠገብ

ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁ ፡- 011 666 3282 / 011 666 2717

 

የቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender