በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የስሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ የማስታወቂያ
ቁጥር A-05/2018
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የስሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡
• የተለያዩ አይነት የታካሚ ቀለብ
• የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች
• የተለያዩ አይነት የቤት ጥገና እና የግንባታ እቃዎች
• በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ (TIN No) ሁሉም ንግድ ፍቃዶች በተናጠል ኮፒ መደረግ አለባቸው እንዲሁም ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ግብር ስለመከፈላቸውና ጨረታ ለመሳተፍ የተፈቀደ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ፣ ወርሐዊ የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችልና ከሚመለከተው መሥሪያ ቤት የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ሆኖ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህርዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND/ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረት የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት /GABANTE/
• የተለያዩ አይነት የታካሚ ቀለብ ብር 11,961.14
• የተሸከርካሪ መለዋዎጫ እቃዎች ብር 116,404.89
• የተለያዩ አይነት የቤት ጥገና እና የግንባታ እቃዎች ብር 124,255,33
ጨረታው 05/06/2018 እስከ 19/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሽጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን 20/06/2018 ዓ.ም ጠዋት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በስ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ዋናው ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ /ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ.ም በአገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማጅ አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ።
የሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ስ.ቁ፡- 058 321 6582/ 058 321 2892/ 09 87 39 48 58
ባህር ዳር
የመከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ
መምሪያ
