በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፣
የጨረታ ሽያጭ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 032፣033፣034/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፣
በዚሁ መሰረት -
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 032/2018 በ13/06/2018 የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች (ፌሮ ብረት፤ ቆርቆሮ፤ ሚስማር)
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 033/2018 በ20/06/2018 የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች(ፌሮ ብረት፤ ቆርቆር፤ ሚስማር)
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 034/2018 በ27/06/2018 የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች(ፌሮ ብረት፤ ቆርቆሮ፤ ሚስማር)
ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች
1. በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።
2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው::
3. በግልጽ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይበተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብርıoo በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ ቀኑ 12 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ የሚገኘው ግቢ ነው::
5. ለግልጽ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፣
6. ተጫራች በግልጽ ጨረታለመጫረት ዕቃዎች ለመግዛት ለሚያቀርበው ዋጋ 5% በጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ (ንግድ ባንከ) የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 3:45 ድረስ በድረዳዋ ሙድአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቁባቸዋል።
8. ጨረታው ከጠዋቱ 3:50 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ጉምሩክ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ላይ ባይገኙም ጨረታ ሳጥን በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡
10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
11. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎቸ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
12. ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
13. ለግልጽ ጨረታ ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ሥም መሞላት አለበት።
14. ተጫራቹ ዋጋ ለሰጠው የብር መጠን በቁጥር እና በፊደል መፃፍ አለበት። ስርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
15. የጉምሩከ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
