የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 002/2018 በጀት ዓመት በሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የተለያዩ ግብዓት አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ 002/2018 በጀት ዓመት በሁለተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የተለያዩ ግብዓት አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የመወዳደሪያ ሰነድ ከአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ - 4 ኪሎ ግንፍሌ ድልድይከፍ ብሎ ወረዳ 7 የግዥ ቡድን 4ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስከርወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ታከስ ከሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ የእቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና
• ለሎት-1 የቢሮ አላቂ ዕቃ----------------10,000.00 ብር
• ለሎት-2 የፅዳት ዕቃዎች-----------------10,000.00 ብር
• ለሎት-3 የደንብ ልብስ-------------------10,000.00 ብር
• ለሎት-4 የህትመት ዕቃዎች------------- 5,000.00 ብር
• ለሎት 5- የእንጨት ስራ የስልጠና እቃ-----------------------5,000.00 ብር
• ለሎት-6 የሆቴል እና የፀጉር ስራ / የህፃናት ማቆያ ዕቃ-------5,000.00 ብር
• ለሎት -7 የከሊኒክ እና የአካል ጉዳተኛ መርጃ----------------5,000.00 ብር
• ሎት-8 የመኪና ዕቃ------------------------------------------5,000.00 ብር
• ሎት-9 የህንፃ ጥገና እቃ------------------------------------5,000.00 ብር
በባንክ በተረጋገጠ Certified Payment Order (CPO) ብቻ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋርማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11 ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ኮሌጁ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ ቫትን ባካተተ መልኩ መሙላት ይኖርባቸዋል ።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን እቃ ለኮሌጁ ንብረት ግምጃ ቤት ያስረከባሉ፡፡
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ በምርመራ ላይ በተቀመጠው መሆን አለበት።
9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ከአሽናፊው ድርጅት ጋር በውል ላይ በተቀመጠው ብዛት ላይ ዋጋ ሳይቀየር 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
ጥብቅ ማሳሰቢያ፦ የጨረታውን ሂደቱን ለማዛባት የሚሞከር ተጫራች ለወደፊቱ በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ ታግደው ያሳያዙት ዋስትና ይወረሳል ፡፡
➢ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ በሰነዱ ምርመራ ላይ በተጠቀሰው መሰረት በእስፒከ ወይም ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ማቅረብ አለበት።
አድራሻ፦ አራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ግንፍሌ ድልድይ ከፍ ብሎ ወረዳ-7
ስልክ ቁጥር:-01-11-26-18-26 ወይም 01-11-11-16-28
የአራዳ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
