በሀድያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች በተያዘው በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሀዲያ ዞን በሻሾጎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀድያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች በተያዘው በጀት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ዝርዝር ዕቃዎቹም፡-
1. የተለያዩ ኮምፒውተሮች
2. የተለያዩ ፕሪንተሮች
3. የተለያዩ ላፕቶፕ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ናቸው።
• በንግዱ ዘርፍ ህጋዊ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
• ለመንግሥት ያስመዘገበው የካፒታል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
• የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ከፋይ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
• የዕቃ እቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፣
• 2 % ታክስ ለመንግሥት መክፈል የሚችሉ፣
• ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመርያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በመያዝ ሻሾጎ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አ/ሥ/ሂደት ቢሮ 12 ቀርበው የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 /አንድ መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
• ተጫራቾች የመወዳደርያ ሀሳባቸውን መ/ቤቱ በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚለው ቦታ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ በማካተት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ ይኖርበታል፡፡
• ተጫራቾች ለተወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፕኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
• አሸናፊዎች ውል በመግባት ዕቃውን እስከ ወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
• ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
• ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መስጠት አይችልም፡፡
• መ/ቤቱ የጨረታውን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
• የተጫራች አለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
• መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 251910494153 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በማ/ኢ/ክ/መ በሀድያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
