የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከዚህ ቀደም ሲገለገልባቸው የነበሩ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የወረቀት መጠረዣ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ቦይለር የላፕቶፕ ባትሪ፣ ኤጋ ቆርቆሮ፣ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ፣ የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች አልሙኒየም/ብረት በር እንጨት በር፣ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የፕሪንተርና የማባዣ ቀለም እና ሌሎችንም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ እና ባሉበት ቦታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ከዚህ ቀደም ሲገለገልባቸው የነበሩ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ የወረቀት መጠረዣ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ቦይለር የላፕቶፕ ባትሪ፣ ኤጋ ቆርቆሮ፣ ቁርጥራጭ ቆርቆሮ፣ የመፀዳጃ ቤት ዕቃዎች አልሙኒየም/ብረት በር እንጨት በር፣ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የፕሪንተርና የማባዣ ቀለም እና ሌሎችንም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ እና ባሉበት ቦታ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ዘወትር በስራ ሠዓት ጃንሜዳ ታቦት ማደሪያ መግቢያ በር ፊት ለፊት ወይም 6 ኪሎ ወደ ፈረንሳይ መሄጃ መንገድ የቀድሞ ማይጨው ጦር ሠፈር የአሁኑ የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ግዢ ዴስክ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ/ ብቻ በመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000003784677 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ስሊፕ በማቅረብ በኮሌጁ ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ የሚሸጡትን ንብረቶች መመልከት ይችላሉ።
2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ሐሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡30 ሠዓት የሚታሸገ እና በዚሁ እለት ከረፋዱ 9፡00 ሠዓት የሚከፈት ይሆናል፡
3. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ግዥ ዴስክ ስልክ ቁጥር 0111-226-507
አድራሻ፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ አዛዥነት እና ስታፍ ኮሌጅ። ጃን ሜዳ ታቦት ማደሪያ መግቢያ በር ፊት ለፊት ወይም 6 ኪሎ ወደ ፈረንሳይ መሄጃ መንገድ የቀድሞ ማይጨው ጦር ሠፈር
የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ
