Tender Detail

Tender Details

  • Company በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ፡ አማራ ክልል : ኢትዮጵያ , Phone: 0336610688
  • Website
  • Deadline31 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-31 00:00:00
  • Categories Building Materials , Construction Materials And Raw Materials

የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በአጣዬ ከተማ አስተዳደር 1ኛ ለሚያሰራው G+3 የአንድ ማእከል ቢሮ ግንባታ የሚሆን ብሎኬት እና ለግንባታው የሚሆን ማተሪያል 2ኛ የኮሪደር ልማት መንገድ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 4

 

የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በአጣዬ ከተማ አስተዳደር 1ኛ ለሚያሰራው G+3 የአንድ ማእከል ቢሮ ግንባታ የሚሆን ብሎኬት እና ለግንባታው የሚሆን ማተሪያል 2ኛ የኮሪደር ልማት መንገድ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም-

•        በዘርፉ የወጣ የንግድ ፈቃድ ያለውና በዘመኑ የታደሰበትን ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችል እንዲሁም መለያ ቁጥር /ቲን/ የተመዘገበበትን መረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡

•        ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን መረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

•        የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡

•        የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

•        ተጫራቾች ለምትጫረቱበት ጨረታ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 1% የጨረታ ማስከበሪያ በCPO፤ ጥሬ ገንዘብ እና ቢድ ቦንድ በአጣዬ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ አብሮ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

•      ተጫራቾች አሸናፈ መሆናችሁ ከተገለፀላችሁ በኋላ ካቀረበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ለኮርደር መንገድ ስራው 25% እና ለግንባታ ማተሪያል ግዥው 10% የውል ማስከበሪያ በCPO፣ ጥሬ ገንዘብ እና ቢድ ቦንድ በማስያዝ ጽ/ቤቱ ያዘጋጀውን ውል በፍትህ ጽ/ቤት የመፈረም ግዴታ አለባችሁ።

•        ለግንባታው ግዥው ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ የሚችለው በኮንስትራክሽን ስራ ዘርፍ ከደረጃ 4 እና በላይ የሆነ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (BC and GC Only) የሆነ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው መሆን አለበት።

•        ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ21 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ከአጣ/ከ/አስ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናሽያል ለብቻ ቴክኒካል ለብቻ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ትችላላችሁ።

•        የጨረታ ሳጥኑ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን በጨረታ መክፈቻው ቀን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት በማሸግ ይከፈታል፡፡

•        በተጨማሪም በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በስራ ላይ ያለውን የግዥ አፈፃፀም መመሪያ እና በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ክ/ቢ-01/02 በቀን 15/09/2014 ዓ/ም በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 179/2003 አንቀፅ 62 ንዑስ አንቀፅ 2 እና በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 አንቀፅ 47 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል

•        ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

•        በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ በተሻሻለው መመሪያ መሰረት ስርዝ ድልዝ ካለው ተጫራቹ ከውድድርውጭ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

•        የጨረታ ሰነዱን ገንጥሎ ማስቀረት የማይቻል ሲሆን የደርጅታችሁን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማድረግ አለባችሁ

•        ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0336610011 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender