Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Address እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አሰ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115548264
  • Website
  • Deadline23 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-23 00:00:00
  • Categories Printing And Publishing

በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን የህትመት አገልግሎት ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 09/2018

 

በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የግዥ ቡድን የህትመት አገልግሎት ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች፟፟፡-

1.     በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin no/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።

2.     የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

3.     የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል፣ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦርጅናል እና 1 የፋይናንሽያል ሰነድ ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ላብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።

4.     የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በቂ/ክ/ከ/ዋ/ሥራ/አስ/ጽ/ቤት (A.A CITY KIRKOS S/C/ADMIN OFFICE) ሂሳብ ቁጥር 1000001455285 ገቢ አድርገው ገቢ ያደረጉበት ደረሰኝ በማምጣት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

5.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ የስራ ቀን በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።

6.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዳቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

7.     ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8.     መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር 9ኛ ፎቅ ስልክ 0115-54-82-64 /011 8-69-43-66

 

በአዲስ አበባ የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

 

Save Tender