Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መ/ቤቶች አገልጎሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መ/ቤቶች አገልጎሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

1.     ሎት 1 የ100ሲሲ ሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃ/ስፔር ፓርት

2.     ሎት 2፡- የእስቴሽነሪ /የጽህፈት መሳሪያና የቢሮ አላቂ ዕቃዎችን

3.     የደንብ ልብስ

4.     የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ኮንፒውተር ፕሪንተርና ሌሎችም

5.     የፈርኒቸር ዕቃዎች

በዚህም መሰረት ማንኛውም ሕጋዊ ድርጅት ወይም ማህበር በግልጽ ጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ፡-በየመስኩ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ አቅራቢዎች ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ፤ በሲፒኦ ወይም በባንክ እስሊፕ (የጦራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አካውንት ቁጥር ላይ 1000258136466 ማስያዝ የሚችሉ፤ ተጫራቾች ሰነዱን ከጦራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ሪከርድና ማህደር ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በጦራ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ዶክመንት በሚገባ በመሙላት 01 (አንድ) ኦርጅናልና 02 (ሁለት ኮፒ ለየብቻ ቴክኒካል ዶክመንት 01 (አንድ ኦርጅናልና 02 (ሁለት ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማስገባትና በማሸግ የድርጅቱን ወይም የማሀበሩን ማህተም በመምታት እና የሚመለከተው የድርጅቱ ወይም የማህበሩ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል በመፈረም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 6፡00 ሰዓት ውስጥ ለጨረታው አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስገቢያው ቀን በተጠናቀቀበት ዕለት የጨረታ ሳጥኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን በ6፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ከደረሰ ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓግልም።

ማሳሰቢያ

1.     ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

2.     አሸናፊ ድርጅ ወይም ማሀበር የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት እና ዕቃ ነው።

3.     የጨረታ ማከበሪያ ከተጠየቀው መጠን አሳንሶ የሚያስገባ ተጫራች የጨረታ መስፈርት ያላሟላ ተብሎ ውድቅ ይደረጋል።

4.     ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ02 ወር /ለስልሳ ቀን ነው፤

ለበለጠ መረጃ በ0954477678/0979198741 ይደውሉ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የጦራ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender