Tender Detail

Tender Details


በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ፋ/ኢ/ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም በመደበኛ እና ካፒታል ከተያዛው በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2. የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3. ፈርኒቸር፣ ሎት4. ሞተር ብስክሌት፣ ሎት5. የጽሕፋት መሣሪያ ዕቃዎችን በተዘጋጀው ጨረታ ሰነድ መሠረት ከአቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


 

የሚዲያ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ፋ/ኢ/ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም በመደበኛ እና ካፒታል ከተያዛው በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 2. የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3. ፈርኒቸር፣ ሎት4. ሞተር ብስክሌት፣ ሎት5. የጽሕፋት መሣሪያ ዕቃዎችን በተዘጋጀው ጨረታ ሰነድ መሠረት ከአቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-

  1. ተጫራቾች በንግድ ዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ቫት የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ማስገባት
  2. ቲን የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ
  3. በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት
  4. ሶስት ፐርሰንት ለመንግሥት ግብር እንደሚከፍሉ ማወቅ አለባቸው።
  5. ግዥው ለዕቃው በሰጡት ዋጋ ማቅረቢያ መነሻ በተናጠል ወይም በጥቅል የሚፈጸም መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎቶች ለዶክመንት የመይመለስ ብር 300 በመክፈል ስ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  7. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ለስ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ብለው ለሎት 1፣ ለሎት 5 ብር 5,000 /አምስት ሺ/ ብር ለሎት 2፣ ለሎት 3፣ 2,000 /ሁለት ሺ/ ብር ለሎት 4፣ 10,000 /አስር ሺ/ ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ማስታወቂያ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡45 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅት እቃውን እስከ ስልጢ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት የጫኝ እና አውራጅ ጨምሮ ማድረስ አለበት፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈው ዕቃ እስከ ሁለት ወር ድረስ ለመሥሪያ ቤቱ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡

 

መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ማሳሰቢያ፡- በጨረታ አሸናፊነት ከተገለጸበት እስከ 7 ቀን ውል ባይገቡ ያስያዙት ሲፒኦ ለመንግሥት ውርስ ተደርጎ የተሻለ ግዢ የሚጠቀም መሆኑን እንገልጸለን።

ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 046882005/32 ይደውሉ

 

በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ፋ/ኢ/ጽ/ቤት

 

Save Tender