Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለኮርፖሬሽኑ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚውል የነዳጅ ዲስፐንሰር ፓምፕ ከነተከላው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን


የነዳጅ ዲስፐንሰር ፓምፕ ለመግዛት

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/4B/2018

 

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2018 በጀት ዓመት ለኮርፖሬሽኑ የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት የሚውል የነዳጅ ዲስፐንሰር ፓምፕ ከነተከላው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ ቲን ነምበር፣ EGP/PPA በአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳሪስ አቦ በሚገኘው ፋፋ የምግብ ኢሚ ጀርባ በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንት (Unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ጥር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነ-ሥርዓት ይከናወናል። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ስልክ: +251911984467 ወይም +25149632090

ፋክስ፡- 0114-421312

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Save Tender

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች (ስክራፕ) የሐራጅ ሽያጭ

READ MORE
በወረጃርሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንገድ መብራት (Street Light Smart Pole) ግንባታ ጨረታ

READ MORE
ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፓወር ፋክተር ኮሬክተር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገጠም ይፈልጋል::

READ MORE
Development Bank of Ethiopia extends the deadline for Rack-Mountable 2KVA UPS (Lot-1), IBM TS-4300 T...

READ MORE