በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለወረዳው ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ደረጃውን የጠበቀ ቢሮ ህንፃ ለማሰራት ስለሚፈልግ የግንባታ ሥራ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን አወዳድረው ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል መንግስት በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለወረዳው ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ደረጃውን የጠበቀ ቢሮ ህንፃ ለማሰራት ስለሚፈልግ የግንባታ ሥራ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾችን አወዳድረው ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት-
1. ደረጃቸው BC/GC 5 በላይ የግንባታ ሥራ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የህጋዊነት መረጃ ከፌዴራል መንግስት ልማትና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ከከልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በ2018 ባጀት ዓመት የተመዘገቡ ወይም የብቃት ማረጋገጫቸውን ያሳደሱ
2. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው፣
3. በዘርፉ የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. TIN Number ያለው
5. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
6. የእቅራቢነት ኦንላይን መረጃ ማቅረብ የሚችል
7. የ2017 ዓ/ም በአዲተር የተረጋገጠበትን ግብር ክሊራንስ ከገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል
8. አስፈላጊውን የግንባታ ዕቃዎችን በራሳቸው አቅርበው መሥራት የሚችሉና ለሥራው በቂ ባለሙያ ያላቸው
9. የጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ ወይም ጥሬ ገንዘብ ሲፕኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንከ ጋራንት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ኦርጅናል ወይም ዋናው ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ መቅረብ አለበት ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ ፍቃዳቸውንና ተጨማሪ እሴት ታከስ ቫት የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት በማቅረብ የጨረታ ዶኩሜንት ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ ብቻ ለዳራማሎ ወረዳ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመከፈል የከፈሉበትን ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ / ለዳራማሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይቻላል፡፡
1. ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የሥራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ስለሳይቱ በማረጋገጥ ነጠላ ዋጋ መሙላት አለበት
2. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ተወዳድረው ከባለሙያ የገበያ ጥናት ከ15% በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ የሥራ ዓይነትና ዝርዝር ሥራዎች ተጨባጭ የወቅቱን የግንባታ ዕቃ ዋጋ ትንተና የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ከነጣላ ዋጋ ትንተና በኋላ ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት የሚጠይቀውን የውል ማስከበሪያ መጠን የመንግስት ገንዘብ ደህንነት ሲባል ከህጋዊ ባንክብቻ ዋስትና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡ ነገር ግን ከባለሙያ ገበያ ጥናት15% በታች ዋጋ በማቅረብ የዋጋ ትንተና አቅርበው ከገበያ ጥናት በታች ያሸነፉ ተቋራጮች ምክንያት በማቅረብ ሥራ ያጓተቱና ውል አቋርጠው የወጡ በጨረታው መሳተፍ ማለት ሆን ብሎ የግዥውን ስርዓት ለማስተጓጓል የሚደረግ ጥረት በመሆኑ በሀገሪቱ ግዥ ህግ መሠረት በህግ እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡
3. የገበያ ጥናት ዋጋ መዋዠቅ ከውል በኋላ በግንባታ አፈፃፀም ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር የኢትዮጵያ ስታትሰቲከስ መ/ቤት ወይም ህጋዊ አስመጭዎች የዋጋ ኢንዴክስ የፋብሪካ ዕቃዎች እያንዳንዱ ተጫራች ማቅረብ አለበት፡፡ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
4. ፋይናነሽያል እና ቴከኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፍ ኮፒዎችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት በሁለተም ፖስታዎች ላይ ስም አድራሻ እና የፕሮጅከቱን ስም በመፃፍ ህጋዊ በሆነ ማህተም በማሳረፍ በመፈረም ፋይናንሻልና ቴከኒካል እያንዳንዱ ሶስት ፖስታ በአንድ ፖስታ ተደርገው ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ በሰም በታሽገ አንድ ፖስታ ታሽገው በሌላ አንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተከተውና የተዘረዘሩ ፅሁፎች እላዩ ላይ ማዕተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት በ31ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በመፃፍ ዳራማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው 25/5/2018 4:00 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ታሽገው በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች አርትሜትከ ቼከ ውጤቱ በጨረታ ከፈታ ወቅት ከተነበበው ዋጋ ከ2% በላይ እና በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ቅናሽ ከ10% በላይ ማድረግ ከጨረታ ውጭ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ፦ ፕሮጀክቱ ያለበት ወረዳ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በ93 ኪ/ሜ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0916298013/0910961784 ይደውሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
