ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና 1ኛ በመደበኛ ካፒታል በጀት ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለቆላና መስኖ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ በአዳዲ- ቀበሌ አዳዲ የማህበረሰብ ኩሬ ቁፋሮ ሥራ ፕሮጀክት ኤክስካቫተር 330 HP ለ200 ሰዓት የሆኑ ማሸነሪዎች ሞዴላቸዉ 2012 እና ከዚያ በላይ ሞዴል የሆኑ የግንባታ ማሽነሪ ኪራይ በጨረታ በማዉጣት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለቆላና መስኖ ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 8/2018
ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና 1ኛ በመደበኛ ካፒታል በጀት ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለቆላና መስኖ ጽ/ቤት በወረዳ ውስጥ በአዳዲ- ቀበሌ አዳዲ የማህበረሰብ ኩሬ ቁፋሮ ሥራ ፕሮጀክት ኤክስካቫተር 330 HP ለ200 ሰዓት የሆኑ ማሸነሪዎች ሞዴላቸዉ 2012 እና ከዚያ በላይ ሞዴል የሆኑ የግንባታ ማሽነሪ ኪራይ በጨረታ በማዉጣት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፡-
- ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN No ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፋ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ እና ለመመዝገባቸው የምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
- የማህበረሰብ ቁፋሮ ሥራው የሚሰራበት ቀበሌ ድረስ በመሄድ መስራት የሚችል
- በዘርፉ የኪራይ ፍቃድ ያለው፡፡
- ማሽነሪዎቹን ከአንድ ሳይት ሌላኛው ሳይት በራሱ ለማጓጓዝ ወይም ለማድረስ ፈቃደኛ የሆነ
- ማሽነሪዎቹን ወደ ሳይት ሲገቡ ጽ/ቤት በሚፈለገዉ ቅደም ተከተል ለማስገባት ፍቃደኛ የሆነ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ለማሽን ኪራይ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ገ/ጽ/ቤት በመሂ1 ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ ፊርማ እንዲሁም የማሽን ኪራይ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛ ቀን ከቀኑ 8:00 በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውሰጥ ማስገባት ይኖርባቸዎል፡፡
- ጨረታው በዚሁ እለት በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት እያግደውም።
- 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግሥት የሥራ ቀን ይከፈታል።
- የሥራ ቦታው አዳዲ ቀበሌ የማህበረሰብ ቁፋሮ ሥራ ፕሮጀከት አዳዲ ቀበሌ ከአዲስ አበባ በአስፓልት 92ኪሜ እና በጠጠር 13ኪ.ሜ እና ከደ/ብረሃን በአስፓልት 28ኪ ሜ እና በጠጠር 13 ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛል።
- በማንኛውም የማሽን ኪራይ ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች እቅራቢው ከሚፈጸምለት ከፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የማሽን ኪራይ አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይ ም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ “ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት''
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የማሽን ኪራይ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው የሥራ ዝርዝር መስረት በውሉ መሰረት ሰርቶ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- ተጫራቾች ከአንድ ጨረታ በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ በተናጠል ወይም በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚከፈትበት ቀን ድረስ በመንግሥት የሥራ ሰዓት ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መሰረዝ ወይም መደለዝ አይፈቀድም።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት ደ/ብረሃን መስመር ላይ ነው።
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6 32-01-47 ወይም 011-6 32-03-04 ደውለው ይጠይቁ፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለቆላና መስኖ ጽ/ቤት
