የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለአገልግሎት የምንጠቀምበትን የተለያዩ ያገለገሉ መኪና እና ማሽነሪዎችን፤ የመኪና መለወዋጫ ዕቃዎችን (spare Parts)፤ ያገለገሉ ጎማዎች፤ ባትሪዎች፤ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን (scrap)፤ ያገለገሉ ፕላስቲክ እና ብረት በርሜሎችን፤ የተለያዩ Auxilary (Mixer, Compressor, Generator)፤ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች (computer Laptop, Printer scanner)፣ የእንጨት እና ፕላስቲክ በሮች እና መስኮቶች፤ የኤሌክትሪክ ፍሎረሰንት የሆኑትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Oromia Construction Corporation (OCC) (የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን)
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/ኦኮኮ-2018
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ለአገልግሎት የምንጠቀምበትን የተለያዩ ያገለገሉ መኪና እና ማሽነሪዎችን፤ የመኪና መለወዋጫ ዕቃዎችን (spare Parts)፤ ያገለገሉ ጎማዎች፤ ባትሪዎች፤ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን (scrap)፤ ያገለገሉ ፕላስቲክ እና ብረት በርሜሎችን፤ የተለያዩ Auxilary (Mixer, Compressor, Generator)፤ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች (computer Laptop, Printer scanner)፣ የእንጨት እና ፕላስቲክ በሮች እና መስኮቶች፤ የኤሌክትሪክ ፍሎረሰንት የሆኑትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዞ በመምጣት የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ቃሊቲ ከመካኒኮች ማሰልጠኛ ፊትለፊት ካለው መ/ቤታችን 1ኛ ፎቅ ከኮርፖሬት ግዢ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ባቀረቡት ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለፁትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል። ለዕቃዎቹ የቀረቡትን ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ያላስያዘ እና በሰነዱ የተቀመጡትን ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ገዝቶ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ3፡00 እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹን ባሉበት ቦታ አዲስ አበባ ፤ አለምገና ፣ ገላን ፤ ጉደር - አምቦ፣ ነቀምቴ ፤ ሀረር፤ መቱ ፣ ጅማ ፤ አርጆ ፤ ባሌ ወልመል ፕሮጀክት፤ ዱከም ፤ ጎሎልቻ፤ ቢሾፍቱ፤ ሱሉልታ፤ ገላን የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ንብረት ዋጋ ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋት 5፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በዚሁ ዕለት 5፡30 ሰዓት ላይ የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ ፡፡
- የኦሮሚያ ኮንስትራከሽን ኮርፖሬሽን ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-439-51-07/09-02-96-40-67/0967-07-48-83 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
