የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎች፣ ባትሪዎችና ሌሎች መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
South Radio and Television Agency (የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት)
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎች፣ ባትሪዎችና ሌሎች መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተገለጹ መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የተሰጠ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁ ያገለገሉ መለዋወጫ ዕቃዎችን ማየት ከፈለጉ የጨረታው ማብቂያ ቀን ከመድረሱ በፊት ባሉት የመንግስት የሥራ ቀናት ወደ መ/ቤታችን መጥተው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ በመያዝ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ወደ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (ቢሮ ቁጥር 10) ቀርበው የማይመሰስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (ቢሮ ቁጥር 11) የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድና የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ማጠቃለያ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በመ/ቤታችን ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 2፡30 ሰዓት ታሽጎ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ 0462125541/ 0462204750/ 0462201091 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
