Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ
  • Address አዲሱ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-54-92-37
  • Website
  • Deadline23 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያው የገንዘብ መጠን በየ ሎቱ የተለያየ ነው።
  • opening date2025-12-23 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Stationery Materials , Electronics Materials , Camera

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የ2018ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የገዥው መለያ ቁጥር 02/2018

 

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የ2018ዓ.ም በጀት ዓመት መግዛት የሚፈልጋቸውን

  • ሎት 1፡- ሴኪዩሪቲ ካሜራ ከነሙሉ ዝርጋታውና ቋሚ የኤሌክትሪክ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪርያ ብር 5,000.00
  • ሎት 2፡- የፅህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4,000.00
  • ሎት 3:- የተለያዩ የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ በብር 4,000.00

ብቃት ያላቸው በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ አገልግሎት መፈፀም ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፣

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገበ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒዩ በቁጥር 1 የተገለጹትን በተጫረቱበት ሎት ብዛት ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 (ፋይናንስ) ቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4:30 በወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ አዲሱ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጪና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
  7. የዘገየ ጨረታና በመክፈቻው ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናቶች የተወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ማስገባት አለባቸው፣ ናሙና ያልቀረበበት ጨረታ ዋጋ አይኖረውም።
  9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ

በልደታ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ ወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ የመ/ቤቱ ስልክ 011-8-54-92-37

 

በልደታ ክፍለ ከተማ የወ/ሮ በለጥሻቸው የህዝብ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender