በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የወረዳው ጤና ጽ/ቤት የተለያዩ ግንባታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል
በማ/ኢ/ክ/መ/ ምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ጨረታ የማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የወረዳው ጤና ጽ/ቤት በአሀዳዊ ዋሽ ፕሮግራም ለመስራት ከታቀዱ ሥራዎች መካከል
ሎት 1፡- የገሬኖጤና ጣቢያ የሠራተኞች ገላ መታጠቢያ ክፍል የእንግዴ ልጅ መቅበሪያና ከኢንስነሬተር የሚወጣ አመድ ማስወገጃ ግንባታ፤
ሎት 2፡- የሱተን ጤና ጣቢያ የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ መፀዳጃ ቤት የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ ግንባታ
ሎት 3፡- የጢያ ጤና ጣቢያ የሠራተኞች ገላ መታጠቢያ ክፍል የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ ኢንስኔሬተር ግንባታ
ሎት 4፡- የእንደቡዮ ጤና ጣቢያ እንስነሬተር እና ከኢንስኔሬተር የሚወጣ አመድ መቅበሪያ እና በጢያ ክላስተር የመንገድ ዳር ሞዴል መፀዳጃ ቤት ግንባታ
ሎት 5፡- አዴሌ ጤና ጣቢያ ደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ በዱግዳ አጠቃላይ ጤና ኬላ የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ በውላውላ ጤና ጣቢያ የንፅህና ግብይት መሸጫ ማዕከል ግንባታ በተጠቀሱት ጤና ጣቢያዎች ግቢ ውስጥ ለመገንባት/የጉልበትና የማቴሪያል አቅርቦት ጨምሮ/በግንባታ ዘርፍ ፈቃድ ባላቸው GC/BC ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በሆኑ አካላቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑ ግብር የከፈለ፣ እና ስለመከፈሉ ከገቢ ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- ቲን ነምበር(TIN No.) ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
- ጨረታው የሚቆየው ከ26/3/2018 ዓ.ም እስከ 16/4/2018 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ለየብቻ ኦርጅናል እና ሁለት ሁለት ኮፒ በማድረግ ሶ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 8 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16/4/2018 ዓ.ም ከሎት 1- ሎት5 በአንድ ጊዜ ከቀኑ 8.00 ሰዓት ታሽጎ ሎት1 በ8:30ሰዓት ሎት 2 በ9:00 ሰዓት ሎት3 በ9:30 ሰዓት ሎት4 በ10:00ሰዓት ሎት5 በ10:30 ሰዓት ሶ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት የግ/ክ/ን/አስ/ሥ/ሂደት በግዥ ኬዝቲም ቢሮ ቁ/ር 8 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ከሎት 1-5 ለእያንዳንዱ 20,000/ሀያ ሺህ ብር /ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሽናፊ ድርጅት አሸናፋው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል።
- አሽናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋ/ይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈጽም በግዥ መመሪያ መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ እንዲሁም ለቅድመ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- በአፈጻጸም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- በወረዳው ውስጥ ፕሮጀክት ይዘው 75% እና ከዚያ በላይ መድረሱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከአሰሪው መ/ቤት ካላቀረቡ መወዳደር አይችሉም።
- ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርበው ሰነድ ላይ ሀሰተኛ ሰነድ ቢገኝ ከጨረታ ሂደት ውጪ ተደርጎ በህግ ተጠያቂ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የግንባታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ/ወ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ እያንዳንዱ ብር 500/ አምስት መቶ ብር / በመክፈል አንድ ተጫራች አንድ ሰነድ ብቻ መውሰድ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ: 046 883 0533/128
የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
