በጕ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሁሉተኛ ዙር የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ ፅህፈት መሣሪያ፣ ህትመት፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የውስጥ ፓርቲሽን ለሕንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እደሳና ጥገና፣ የሰራተኛ ካፍቴሪያ ቋሚ የህከምና እታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
የሁለተኛ ዙር ዕቃ ግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በጕ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሁሉተኛ ዙር የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ ፅህፈት መሣሪያ፣ ህትመት፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የውስጥ ፓርቲሽን ለሕንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እደሳና ጥገና፣ የሰራተኛ ካፍቴሪያ ቋሚ የህከምና እታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለዚህም፡-
1. ማንኛውም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለና በአቅራቢዎች ሊስት የተመዘገበ በራሱ ትራንስፖርት ጤና ጣቢያው ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
2 ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቶች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ የዕቃውን ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት የደንብ ልብስ 3,411 ሎት 2 የፅህፈት መሣሪያ 2,000 ሎ-13 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 1500፣ ሎት4 /ፕላንት ማሽነሪ ለመሳሪያዎች ግዥ 4,000 ሎት5 የዕዳት ዕቃዎች 2,890 ሎት6 የውስጥ ፓርትሽን) ለሕንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች እደሳና ጥገና 5.000 ሎት7 የሰራተኛ ካፍቴሪያ 26,485 ሎት 8 ህትመት 1500 ሎት 9 ቋሚ የህክምና እታ 10,000 በጤና ጣቢያው ስም በየሎት የተገለፀውን CPO (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው፣ ተደምሮ የሚመጣው CPO (ሲፒኦ) ተቀባይነት የለውም፡፡
3. አሸናፊ ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ የሚውል የጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ማንኛውም ተጫራች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ጤና ጣቢያው ድረስ በመምጣት አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 406 ግዥ ከፍል ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም ግን በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ በዋስትና ደብዳቤ ሰነዱን በነፃ መውሰድ የሚችሉ ይሆንና ነገር ግን ድርጅታቸው በማያመርቱባቸው እቃዎች/ሎቶች ላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ እና የጨረታ ማስከበሪያ CPO (ሲፒኦ) ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ሰነዱን የሚወዳደሩበትን ሎት ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ/ በየሎቱ ታሸጎ/በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው 10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
7. የጨረታ ሠነዱን ዋጋ ሞልተው ለማስገባት ሲመጡ በቅድሚደ ናሙና መቅረብ ባለባቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረቱበትን እቃ መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው አሙቱን ሙሉ ማቅረብ የሚችል፡፡
9. ጤና ጣቢያው የዕቃውን ብዛት እንደአስፈላጊነቱ ከውል በፊትም 20% እና ከውል በኋላ 25% የመጨመርወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. መስሪያ ቤቱ የዕቃውን አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው እስከ 6 ወር ድረስ የእቃውን 25% በንጥል ዋጋ ተጨማሪ ግዥ ትዕዛዝ ሰጥቶ ግዥ መፈፀም ይችላል፡፡
11 መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ሥላሴ ቤ/ክርስቲያን ሳይደርሱ በስተግራ በሚያስገባው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በቀድሞው ቀበሌ 23/08 ባሁኑ ወረዳ 6 አጠገብ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911899632 / ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉ/ክ/ከተማ አዲስ ሕይወት ጤና ጣቢያ
