Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security40,000.00
  • opening date2025-12-18 00:00:00
  • Categories Security Service , Cctv Camera

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የደህንነት ካሜራዎች /Security Camera/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/09/2018(NCB)

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት የደህንነት ካሜራዎች /Security Camera/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፤
  2. የጨረታ ሰነዱን ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የኢ.ኤ.አ ፕሮጀክቶች ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. አ.አ.ኤ.አ.ፕ ወይም EEU-UEAP ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/09/2018 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ታህሳስ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ. ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ከካቴድራል መብራት ወደ አራት ኪሎ በሚወስደው መንገድ ከኤንሪኮ ኬክ ቤት 150 ሜትር ርቀት በሚገኘው ማህበራዊ ዋስትና አዲሱ ህንፃ 11ኛ ፎቅ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም ታህሳስ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀነ 8፡30 ላይ ይከፈታል፣
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘውትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት 7፡00-11፡00 እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ።
  7. የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
  8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111 263 159 መደወል ይችላሉ፡፡

 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መ/ቤት ፕሮጀክት ፖርቲፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት

Save Tender