Tender Detail

Tender Details


የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 005/ሽያጭና አገልግሎት/18 ዓ.ም

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2018 በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የሽያጭና የአገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል፡፡

  • 1ኛ. ለምግብነት የሚውል ጤፍ እና የእህል ብጣሪዎች ሽያጭ ለመጀመርያ ጊዜ
  • 2ኛ. የዘር መቋጠርያ ፖሊ ባግ ግዥ ለሶስተኛ ጊዜ
  • 3ኛ. የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ
  • 4ኛ. ያገለገለ ባለ 100 ኪ/ግ ሚዛን ሽያጭ ለሶስተኛ ጊዜ

በዚሁ መሰረት-

  • ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ሕጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  • የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
  • የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
  • ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች በሚዘጋጀው የጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046 220 1752/2285/2117 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት

 

Save Tender