በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለጣ/ወ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በመደበኛ እና በተራድኦ በጀት ከዚህ በታች በየሎቱ በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ግዥ/ንብ/አስ/004/2018
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለጣ/ወ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በመደበኛ እና በተራድኦ በጀት ከዚህ በታች በየሎቱ በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም የሚፈልግ ሲሆን ግዥው የሚፈጸመው በየሎቱ ዓይነት በጥቅል ሲሆን ለከፊሎቹ ዋጋ መስጠት ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል።
ሎት 1 የተለያዩ ዓይነት የግንባታ ቁሳቁስ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 ሎት2 የተለያዩ ዓይነት ኤችኤዲፒ ፓይፕ (HDP PIPE) ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00፣ ሎት 3. የተለያዩ ዓይነት የጽሕፈት መሣሪያ ግዥ ብር 20,000.00 ብር፣ ሎት 4. የተለያዩ ዓይነት የፅዳት እቃዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 ሎት 5. የተለያዩ ዓይነት የደን ዘር ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 ብር እኛ ሎት 6. የተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00 ብር ማስያዝ አለባችሁ።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን ነምበር/ ፣ የምታቀርቡት ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዝርዝር ጉዳይ የያዘ የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ከሎት1 እስከ ሎት 6 ያለውን የማይመለስ ብር በሚወዳደሩበት ዘርፍ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) ጣ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ያሉት ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም ስም ፊርማ አድራሻ ስልከ ቁጥር በማስፈር ኦርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው በደብረሲና ከተማ ፀደይ ባንክ ሕንፃ ጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ኃላፊ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከሎት - 1 እስከ ሎት 6 በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡29 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥኑ 4:30 ሰዓት ይታሸግና በዚሁ ቀን 4፡45 የሚከፈት ሲሆን ቀኖቹ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
- ነጠላ ዋጋውና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ካለ የነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾች ምርጫ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ለመሥሪያ ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ1 በጥሬ ገንዘብ በምትወዳደሩበት ከላይ በየሎቱ ለተጠቀሱት ዘርፍ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማሸግ ማስያዝ ይጠበቅባቸኋል።
- ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- አሸናፊው ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ግዥ በጣ/ወ/ደ/ሲና ከተማ በ4ም ፑል ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ በባለሙያ እየተረጋገጠ በስሙ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይችላሉ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116800432/0116800068/ ደውለው ይጠይቁ።
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
